Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

cfsa

Child and Family Services Agency
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

Amharic (አማርኛ)

Amharic (አማርኛ)
This page contains information about Child and Family Services for Amharic speakers.

የልጅ እና ቤተሰብ  አገልግሎት ኤጀንሲ

ተልእኮ:    
የልጅ እና ቤተሰብ አገልግሎት ኤጀንሲ (ሲኤፍኤስኤ) (CFSA) በዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ ጉዳት የደረሰባቸው እና ችላ-የተባሉ ልጆች ሴፍቲ፣ ቋሚ ሁኔታ እና ደህንነት ለማሻሻል ይሰራል፤ እንዲሁም፣ ቤተሰቦቻቸውን ለማጠናከር። 

ዋና ዋና ፕሮግራሞች:

የልጅ እና ቤተሰብ አገልግሎት ኤጀንሲ (ሲኤፍኤስኤ) (CFSA)  ለስምንት ዋና ዋና እሴቶች ይተጋል:

ቤተሰቦች ሌሎች እንዲገነዘቧቸው፣ ዋጋ የመሰጠት፣ የመበረታታት፣ እና የመጎልበት መብት አላቸው። ቤተሰቦች እነርሱን የሚነካ ውሳኔዎች ሲወሰዱ ሁሌም ድምጻቸውን ያሰማሉ።
ሁሉም ልጆች እና ወጣቶች የደህንነት(ሴፍ) የመሆን መብት አላቸው።
ልጀችና ወጣቶችን ደህንነት(ሴፍ አርጎ) ለመጠበቅ የሕብረተሰቡ ትበብሮች ወሳኝ ናቸው።
ልጆች፣ ወጣቱ እና ቤተሰቦች አዎንታዊ ውጤቶችን እንዲያስመዘግቡ ለመርዳት  የልጅ ደህንነት መጠበቂያ አሰራር እና አገልግሎታችን ዋነኛ እገዛ ይዞ ይመጣል።
ልጆች እና ወጣቶች ለማደግ፣ ለመበልጸግ፣ የአካል እና የአእምሮ ጤናማ ለመሆን፣ ለመማር እና ለስኬታማ የአዋቂነት ዘመን ለመዘጋጀት እድሎችን ማግኘት ይገባቸዋል።
ልጆች እና ወጣቶች በተቻለ ፍጥነት፣ ያለምንም ቅድመ ሁናቴ ከሚወዳቸው ቤተሰብ ጋር ቐሚነት የማግኘት አንገብጋቢ ፍላጎት አላቸው።
ልጆች፣ ወጣቶች እና ቤተሰቦች በታሪካቸው፣ በወጋቸው እና በባህላቸው መሰረት ግንዛቤ መሰጠት እና መከበር ይገባቸዋል።
የልጆች የደህንነት ሲስተም ምርጥ አሰራሮች እና የማያቋርጥ የጥራት ማሻሻል የምናገለግላቸው ሕይወት ላይ አዎንታዊ ለውጥ ለማምጣት ይረዳል።
አገልግሎቶች:
የጀርባ  ታሪክን ማረጋገ ጥ (Background Checks)፡ የልጆች መከላከል መዝገብ( Child Protection Register (CPR) በሚስጥር የሚያዝ፣ በዲሲ ውስጥ ልጆችን በመጉዳት ወይም ችላ በማለት የሚታወቁ ወይም ጠንካራ ጥርጣሬ የታደረባቸው ሰዎች መመዝገቢያ ነው።
ሲኤፍኤስኤ (CFSA) እንባ ጠባቂ : ድምጾትን ያሰሙ፤ ሲኤፍኤስኤ(CFSA)  በኤጀንሲው አገልግሎት ወይም ውሳኔ አለመርካትን ማሳየትን ለመርዳት  በርከት ያሉ መንገዶችን ያቀርባል።
የጉዲፈቻ ወላጅ: በገዛ ቤታቸው ደህንነት(ሴፍቲ) ማግኘት ለማይችሉ  የዲሲ ልጆች እና ወጣቶች ሲኤፍኤስኤ(CFSA ) ሴፍ ሁኔታን ያቀርባል።
የልጅ መጎዳት እና ችላ መባል ምርመራ: ሲኤፍኤስኤ(CFSA)  በልጆች ደህንነት ሁኔታ ምርመራ በሚደረግበት ግዜ ቤተሰቦች ምን መጠበቅ እንዳለባቸው እንዲረዱ መረጃን ይሰጣቸዋል።
የአያት ፕሮግራም(Grand Parent Program)፡ የአያት ተንከባካቢዎች ፕሮግራም የቤተሰብን ህብረት ይደግፋል እናም ልጆች የልጆች ደህንነት መጠበቂያ ሲስተም ውስጥ እንዳይገቡ ይረዳል።
ሃላፊነት ያለባቸው ጠቐሚዎች ስልጠና (Mandated Reporter Training): ሃላነት ያለባቸው ጠቋሚዎች(Mandated reporters) በዲሲትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ ልጆች መከላከል ላይ ወሳኝ አካል ናቸው። 
አዲስ ለተወለዱ ልጆች ምቹ መሸሸጊያ (Safe Havens for Newborns): በቤታቸው መቆየት ለማይችሉ ልጆች እና ወጣቶች ሲኤፍኤስኤ(CFSA)  ደህንነታቸው የሚጠበቅበት(ሴፍ) ሁኔታን ይሰጣል።
በፈቃደኝነት የማደጎ(የፎስተር ኬር)መመዝገቢያ (Voluntary Foster Care Registry): በአሁኑ ወቅት ወይንም ከዚህ በፊት የማደጎ ወጣቶች እና የደም ቤተሰቦቻቸው በዲስትሪክቱ የማደጎ ማሳደጊያ ውስጥ የተለያዩ አሁን ለመገናኘት መንገድ አላቸው።
ጠቅላላ መረጃ: ስለ ማህበራዊ አገልግሎቶች፣ መረጃዎች(ሪሶርስ)  እና የደህንነት መሸሸጊያ( safe havens) የሚፈልጉትን መልሶችን ያግኙ።

የትርጉም አገልግሎት: 
ለቃል/የወረቀት ትርጉም ጥያቄዎች እባኮን ከታች ካሉት ጛዶች አንዳቸውን ያግኙ፦

የቋንቋን ማግኛ (Language Access) አቀነባባሪ
ሚስ ኢኒስ ስፕንስ (Ms. Grenetta Wells): (202) 321-0062, [email protected]

የቋንቋን ማግኛ (Language Access) አቀነባባሪ ረዳቶች:
ሚስ ኢኒስ ስፕንስ (Ms. Christina White): (202) 497-4387, [email protected]

አድራሻ:   
የልጅ እና ቤተሰብ አገልግሎት ኤጀንሲ (Child and Family Services Agency)
200 I Street, SE
Washington, DC 20003
ስልክ: (202) 442-6100
ፋክስ: (202) 727-6505
 

የዲሲ የልጅ እና ቤተሰብ አገልግሎት ኤጀንሲ
DC Child and Family Services Agency

● ለልጅ መጠቃት እና ቸልተኝነት ቀድሞ ደራሾች 
  
● ቤተሰቦችን በማጠንከር ለማህበረሰቡ አስተዋጽኦ ማድረግ

በዲስትሪክቱ፣ የዲሲ የልጅ እና ቤተሰብ አገልግሎት ኤጀንሲ (ሲኤፍኤስኤ)
(DC Child and Family Services Agency (CFSA))፣ ተጠቂ ልጆችን እና
ለጥቃት(abuse) እና ለቸልተኝነት(neglect) የተጋለጡ ልጆች የመከላከል ህጋዊ ስልጣን አለው።
በአገሪቱ ዙርያ እንደሚገኙ የህዝብ የልጅ ድጎማ(ዌልፌር) ኤጀንሲዎች፣ ሲኤፍኤስኤ (CFSA)
በአራት ዋነኛ ተግባሮች ልጆችን ይከላከላል።

ሪፖርቶች መውሰድ እና መመርመር: ሲኤፍኤስኤ (CFSA) የልጆች መከላከያ አገልግሎት (CFSA Child Protective Services) በአከባቢው የህዝብ ልጅ መከላከያ ሲስተም የመግቢያ በር (gateway) ነው። ሲፒኤስ (CPS) በዲስትሪክቱ ስለ ታወቁ ወይም የተጠረጠሩ፣ እስከ 18 ዓመት ስለሆናቸው  ልጆች የጥቃት እና ቸልተኝነት ሪፖርቶች፣ በቀን ለ24ት ሰዓታት  በዓመት 365 ቀናት ፣ ይወስዳል። ሪፖርቱ፣ በህጉ በተተረጎመው መሰረት አንድ ልጅ በጥቃት(abuse) ወይም በቸልተኝነት(neglect) እየተጎዳ እንደሆነ ሲያሳይ፣ ሲፒኤስ (CPS) ሪፖርቱ እውነት ወይም ሀሰት እንደሆነ ለመወሰን ምርመራ ማድረግ አለበት። መርማሪ ሶሻል ወርከሮች (Investigative social workers)፣ በወላጆች፣ በአሳዳጊዎች፣ ወይም በሌሎች በወላጅ ደረጃ የሚሰሩ አካላት የሚደርሱት የልጅ ጥቃት እና ቸልተኝነት የሚመለከቱ ሪፖርቶች በዲስትሪክቱ ሲያጋጥሙ ይመለከታል።

ቤተሰቦችን ማጠንከር: የልጅ ድጎማ (ዌልፌር) ልዩ ነው፣ ምክንያቱም፣ ተቀዳሚ ደንበኞቻችን- ልጆችን- ማገልገል ማለት ወላጆቻቸው ወይም እንክብካቤ የሚሰጡአቸውን መደገፍ ማለት ነው። ሲኤፍኤስኤ (CFSA) የጥቃት እና ቸልተኝነት ተጠቂ ልጆችን ሲለይ፣ ከሲኤፍኤስኤ (CFSA) ወይም ከሲኤፍኤስኤ (CFSA) ጋር ውል ካላቸው የግል ድርጅቶች የወጡ የሰለጠኑ ሶሻል ወርከሮች ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመስራት የህጻናቱን ደህንነት ለመጠበቅ ይሰራሉ። ቤተሰቦችን፣ ልጆቻቸውን አደጋ ላይ የሚጥሉ የረጅም ግዜ ውጣ ውረዶች እንዲፈቱ የሚያስችሉአቸው አገልግሎቶች ጋር እናገናኛለን። ግማሽ አከባቢ የሚሆኑ ጉዳዮቻችን፣ ሶሻል ወርከሮች ልጆች በቤት ውስጥ ደህንነት እና መልካም አያያዝ እንደሚያገኙ መከታተልን ያጠቃለሉ ናቸው። 

ለልጆች ዋስትና(ሴፍ) የሚሰጡ፣ ግዚያዊ ቤቶች ማቅረብ: የአንድ ቤተሰብ ቤት (ወይም ሌላ የመኖርያ አከባቢ) ለከፍተኛ አደጋ የሚያጋልጥ ከሆነ፣ ሲኤፍኤስኤ (CFSA) ልጆቹን ዋስትና  ወዳለበት ሁኔታ የመውሰድ ስልጣን አለው። ከዛ ወዲያውኑ ከዲስትሪክቱ የቤተሰብ ፍርድቤት (District’s Family Court) ስምምነት እንጠይቃለን።. በአብዛኛው፣ በቤታቸው ደህንነት ሊያገኙ ለማይችሉ ልጆች ዘመዶቻቸው ይወስዱዋቸዋል። ሲኤፍኤስኤ (CFSA) የማደጎ ወላጆችን ይመለምላል፣ ያሰለጥናል እና ፈቃድ ይሰጣል፣ በተጨማሪ የልጆች የቡድን ቤቶች (group homes) (እና ሌሎች ዋስትና ያላቸው ቦታዎች) ፈቃድ ይሰጣል፣ ይከታተላል፣ ውልን ይቀጥላል። 

ልጆች ከቤተሰብ ጥምረት ጋር ሲሆኑ ነው ከሁሉም በተሻለ መልኩ የሚያድጉት። በዚህም ምክንያት ልጆችን ከቤት መለየት በአብዛኛው ግዚያዊ ነው የሚሆ። ግቡ፣ ወላጆች ራሳቸው ልጆቻቸውን መከላከል እና መንከባከብ እንዲችሉ፣ የወላጆችን ቀውሶች በመፍታት መደገፍ እና ችግሮችን መወጣት እንዲችሉ ማድረግ ነው። ነገር ግን፣ ወላጆች ልጆቻቸውን ለመከላከል የማይፈልጉ ወይም የማይችሉ  ከሆነ፣ ሲኤፍኤስኤ (CFSA) እና የቤተሰብ ፍርድቤት ለልጆቹ ከተወለዱባቸው ቤቶች ውጪ ቋሚነትን ይፈልጋሉ።

ልጆች ቋሚ መኖሪያ እንዲኖሯዋቸው ያረጋግጡ: ሁሉም ሰው ቤተሰብ ያስፈልገዋል። ሲኤፍኤስኤ (CFSA) ጉዲፈቻ ለመውሰድ ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎችን ይመለምላል ያሰለጥናልም። አብዛኛዎቹ ከልጆች ድጎማ (ወልፌር) ሲስተም ወጥተው ወደ ጉዲፈቻ ቤት ለመግባት ተስፋ የሚያደርጉ የአከባቢ ወጣት/ልጆች ዕድሜአቸው 8 እና ከዛ በላይ ናቸው። አብዛኛዎቹ ከወንድሞቻቸው እና እህቶቻቸው ጋር ነው ጉዲፈቻ እንዲወሰዱ የሚፈልጉ። በሲኤፍኤስኤ (CFSA) በኩል ጉዲፈቻ የሚወስዱ ሰዎች በአብዛኛው፣ ለገንዘብ እና ሌሎች ድጋፎች ብቁ ይሆናሉ። ህጋዊ  የወላጅነት መብቶች በህጋዊ መንገድ ሳያቆሙ ለልጆች ቀዋሚ ቤት ማቅረብ ለሚፈልጉ ዘመዶች (ወይም ሌሎች) አሳዳጊነት/ሞግዚትነት ከጉዲፈቻ አማራጭ መንገድ ነው።